የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማዉ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች እንዲሁም ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስቀረብ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሞሉ ሁሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የ2018 የበጀት አመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚሞሉትን የእቃን ጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሰራት በጥሬ ገንዘብ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን ዋና በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት/ግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ የሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ3፡30-4፡00 ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዱ የተዘረዘሩት አቃዎችን በሙሉ የመሙላት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ የአንድንም የእቃ ዋጋ ዝርዝር አለሞሙላት ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር (በሎት) ይሆናል፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰ እቃ መሰረዝ መደለዝ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፍቸውን እቃዎች መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አቅርቦቶች ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው በተጠየቀው (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ጥራቱ ተጠብቆ ካላቀረበ በመመሪያ መሰረት መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ በዝርዝሩ የተጠቀሱትን እቃዎች ብዛት 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

