በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እንዲሁም 3 የግንባታ እቃዎች አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዳቸው በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር ለተራ ቁጥር 1. ብር 60,000 /ስልሳ ሽህ ብር/፣ ለተራ ቁጥር 2 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለተራ ቁጥር 3 ብር 80,000 /ሰማኒያ ሽህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማሲያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት ጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 1 በ16ኛው ቀን አስራ ስድስተኛው /ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ያወጡት ውጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን እቃዎችን ወረዳው ድረስ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ የሚችልና ለፍትህም ሆነ እና ለማንኛውም አገልግሎት የሚከፈለውን ውጭ እራሱ የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይለያል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ አቤቱታ /ቅሬታ/ ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን እቃዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡
- አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት 3 በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ግዥ ፈጻሚው አካል ግዥውን ለመገምገም፣ ለማጽደቅ፣ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና ከአሸናፊ ድርጀቱ ጋር ውል እስከሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆይበት ለ40 ቀን ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 664 04 54 /002 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

