ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቆላድባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች የ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃ ሎት 3 የተዘጋጅ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለየአንዳንዱ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በቆላድባ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 18 ከህዳር 8/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 22/2018 ዓ.ም ተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  6. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቆላድባ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በ16 ኛው ቀን በተከታታይ ቀናት እስከ ህዳር 23/2018ዓ.ም 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ህዳር 23/2018 ዓ.ም በ16 ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 18 በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በለሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
  9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  10. ማንኛዉም ተጫራች /ተወዳዳሪ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በፍጥነት ዕቃውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. ማንኛውም ተወዳዳሪ የጽ/መሳሪያ፣ኤሌክትሮኒክስ እቃ እና የተዘጋጀ ፈርኒቸር እቃ ጽ/ቤቱ ያቀረበውን (ስፔስፊኬሽን) በትክክል በማየት መወዳደር ይኖርበታል፡፡
  12. ጨረታዉ የሚከፈተዉ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የካላንደር በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ በስራ ሰዓትና ቀን የሚከፈት ይከፈታል፡፡
  13. አሸናፊነቱ እንደተገለፀ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ በምስ/ደ/ወ/ፍ/ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መውሰድ የሚችል እና ሁሉንም እቃዎች ቆ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማምጣት አለበት፡፡
  14. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 18 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 07 95 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም፡፡

የቆላድባ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here