የአምባሰል ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ:- ሎት 1 የጽህፈት መሳርያዎች፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ አልባሳት፣ ሎት 3 ጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት 5 ቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች እንዲሁም ሎት 6 ፕላንትና ማሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታዉ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ፡-
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፤ የዘመኑ ግብር የከፈላችሁ እና ቲን ያላችሁ፡፡
- በእያንዳንዱ የሎት ምድብ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ለሆኑ ማንኛውም ግዥ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደረበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በማስላት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የክልል የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታው ውድድር በየሎቱ ስለሆነ በሚወዳደሩበት የሎት ምድብ ዘርፍ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ዋጋ በሙሉ መሞላት አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከመጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ 4:45 ይከፈታል፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው ተጫራቾች በተገኙበት ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል በመገኙት ወይም በስልክ ቁጥር 09 21 51 89 44 /033 224 03 74 በመደወል መጠየቅ ይችላኩ፡፡
የአምባሰል ወረዳ ፍርድ ቤት

