ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
110

የግዥ መለያ ቁጥር አብክመ ሳቴኮ/ግ/ጨ/ 01 /2017

የአብክመ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ለ2017 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ፡- ሎት 1. የፅህፈት እቃዎች፣ ሎት 2. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3. የኮምፒዩተርና ኢንተርኔት እቃዎች፣ ሎት 4. የብስክሌት መለዋወጫዎች፣ ሎት 5. የተሸከርካሪ ጎማዎች፣ ሎት 6. የተሸከርካሪ ዲኮርእቃዎች፣ ሎት 7. የኤሌክትሪክና ኮንስትራክሽን መሳሪዎች፣ ሎት 8. የውሃ መስመር መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የሚወዳደሩበት ግዥ ጥቅል ዋጋ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ዋጋ የሞሉበት ቅፅ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1 – 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በተቋሙ ዋ/ገንዘብ ያዥ ቢ/ቁ/02 በመምጣትና የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ / በመክፈል  ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ግዥ (ሎት) ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ   ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል፡፡

አሸናፊው የሚለየው በሎት (ጥቅል) ዋጋ ይሆናል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582264135 መደወል ይችላሉ፡፡

የአብክመ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here