ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
79

የእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለእብናት ወረዳ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃ ሎት 3 የጽዳት እቃ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ ትችላላችሁ፣

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ እብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ግቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ ኦርጅናል ሰነድ እብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ባዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ ለ15 ቀን ይቆያል፡፡ በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  7. አሸናፊው ለስራ በተፈለገበት ስዓት ለ3 ቀናት ተጠብቆ ካልቀረበ በመመሪያ መሰረት መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር በሚሞሉበት ሰዓት ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ መሆን የለበትም ሥርዝ ድልዝ ያለው ከሆነም ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ዉስጥ አንዱን ያልሞላ ከጨረታ ወጭ ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊ የሚለየዉ በጥቅል ድምር ይሆናል፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 08 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  13. አሸናፊው አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  15. ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 20 ቀን ይሆናል፡፡
  16. አሸናፊዉ ድርጅት በወጣዉ ጨረታ መሰረት ከሚያቀርባቸዉ ዕቃዎች ውስጥ ተቋሙ በሚፈልገው ልክ ናሙና ለሚያስፈልጋቸዉ እቃዎች ናሙና ማቅረብ እና በአቀረባቸዉ ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችል፡፡
  17. አሸናፊዉ ድርጅት እታዉን የሚያቀርበዉ እብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
  18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 440 06 06 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here