በአብክመ በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኙው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1 ዩኒየኑ ከአቀፋቸው መሰረታዊ ህ/ስ/ማህበራት ወደ ዩኒየኑ መጋዝን ድረስ የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት የአገልግሎት ግዥ፣ ሎት 2 የዶቄት ፋብሪካ መለዋወጫ ግዥ፣ ሎት 3 ፈርኒቸር ግዥ፣ ሎት 4 የመኪና ጎማና መለዋወጫ ግዥ፣ ሎት 5 የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ፣ ሎት 6 የጥበቃ የደንብ ልብስ ሰፌት የአገልግሎት ግዥ፣ ሎት 7 የጽህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 8 የጽዳት እቃዎች ግዥ፣ ሎት 9 የአፈረ ማዳበሪያ ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የአገልግሎት ግዥ፣ ሎት 10 የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የአገልግሎት ግዥ፣ ሎት 11 የመጋዝን ጥገና የአገለግሎት ግዥ፣ ሎት 12 የአገለገለ እቃ ሽያጭ፣ ሎት 13 የቢሮና የሱቅ ኪራይ የአገልግሎት ግዥ እና ሎት 14 የኤሌክትሪክ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሽናፊው የሚጓጓዘውን ማጓጓዝ፣ የሚገዛውን መግዛት፣ የሚጠገነውን ማስጠገን እና የሚሸጠውን መሸጥ ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ግልጽ ጨረታ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 /ሶስት መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፡፡ በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ቅዳሜ ዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተወዳዳሪዎች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፡፡ አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ ይምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡
- የሰብል ማጓጓዝ ጊዜው እስከ ሀምሌ 30/2018 የሚቆይ ሲሆን ሰብል የመርክበ ኃላፊነት የዩኒየኑ ወይም የመሰረታዊ ህ/ስ/ማህበሩ የሚወክለው ንብረት ክፍል ሲሆን የማስጫኛና ማውረጃ ወጭ አሸናፊ ትራንስፖርተር አይከፍልም፡፡ የትራንስፖርት ማጓጓዣ ወጪ እና መንገድ ላይ የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያዎች አሸናፊ ትራንስፖርት ይሸፍናል፡፡
- የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት ተጫራች በስማቸው የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት በኪሎ ሜትር በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ከመነሻው እስከ መራገፊያው ድረስ ያለው ኪሎ ሜትር ሲሞላ በትንሹም ቢሆን ሊቀንስና ሊጨምር እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ቦታውን አውቃችሁ እንድትሞሉ፡፡
- የአፈረ ማዳበሪያ ማከማቻ መጋዝን ኪራይ ለስድስት ወር የሚቆይ ሲሆን የማከራየት ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፤ የመያዝ አቅሙ ሀምሳ ሺህ እና በላይ የሆነ ሁኖ እንደአስፈላጊነቱ የሚራዘም ይሆናል፡፡ የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ ለአራት ወር የሚቆይ ሁኖ የመያዝ አቅሙ ሰላሳ ሺህ እና በላይ የሆነ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ የሚራዘም ይሆናል፡፡ የመጋዝን ኪራይ አሸናፊ የሚለየው በአንድ ኩንታል ዋጋ ሲሆን ዋጋሚ የሚሞላው የአንድ ኩ/ል ዋጋ ታሳቢ ተደርጎ ይሞላ ምክንያቱም አሸናፊ የሚለየው ርዝመት*ቁመት*ወርድ-15%/1.8*10= መጋዝን የመያዝ አቅም ስለሚሰጥ የተሞላው የብር መጠን ሲካፈል መጋዝኑ የሚይዘው የኩ/ል መጠን በማድረግ አሸናፊ የሚለይ ሲሆን የመጋዝኑ የመያዝ አቅሙ ዩኒየኑ በሚያዋቅረው ኮሜቴ ተለክቶ በሚገኘው መሰረት ይሆናል፡፡ የምንከራየው የመጋዝን ኪራይ ብዛት ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሁኖ አሸናፊውን በቅደም ተከተል ይሚያዝ ይሆናል፡፡
- አሽናፊው የአሽነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ሊያቀርብ ነው፡፡ ለስራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊ የሸፍናል፡፡ የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
- ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ በተገለጸው ሎት 12 ከሀ-ሐ ሥር ከጨረታ ሰነዱ ላይ በሚዘረዘረው መሰረት መርጦ መሙላት ይቻላል፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በሥልክ ቁጥር 09 10 63 46 46 / 09 11 59 05 34 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.

