በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤትግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥ/ሂደት አገልግሎት የሚውሉ 1. ጄኔሬተር፣ 2. ቶታል አስቴሽን Total station እና 3ኛ. ኮምፒውተር እና ፕሪንተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ጨረታው በአይነት መሆኑን አውቃችሁ ከዚህ በታች የተረዘሩትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባችኃል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ዳንግላ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ግዥ ቢሮ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለተራ ቁጥር 1 ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለተራ ቁጥር 2 ብር 50,000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ እንዲሁም ተራ ቁጥር 3 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቀ ባንኮች የሚሰጥ እንጂ ምርጫቸው (በሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በመስሪያ ቤቱ ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ባንክ ሂሳብ ቁጥር የሚያስግባ እና ዲፖዚት ስሊፕ ማቅረብ የሚችሉ ወይም በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ የሚያደርግ እና ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 25 በመቶ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ እና በባንክ በመ/ቤቱ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረግ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስም፣ አድራሻ ፊርማ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ በተለየ ፖስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ግዥዎች ቢሮ ለጨረታ ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡00 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- በ16 ተኛው ቀን እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በ 4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ሙሉ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በተጨማሪ በአብክመ ግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር መረጃ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 088 221 16 10 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የዳንግላ ከተማ አስተዳር ገንዘብ ጽ/ቤት

