ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
30

በደቡብ ጎንደር ዞን የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መሪ የተለያዩ ግዥዎችን ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 3 የመኪና ጎማ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የገንዘብ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመ/ኢ/ከ/አስ/ገ/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የእቃውን ዝርዝር መግለጫዎች (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደርበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ ላይ እና ፖስታው ላይ የንግድ ድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለበት፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ (ኢንቨሎፕ) መ/ኢ/ከ/አስ/ገ/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው በ16ኛው ቀን ሎት 1፣ 2 እና 3 ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡15 ይከፈታል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በ16ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ እስከ ሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ጨረታውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች በዝርዝር ወይም በሎት ከቀረቡት እቃዎች ውስጥ ዋጋውን ነጥሎ መሙላት አይችልም፡፡ ነጥሎ የሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  14. የጨረታ አሸናፊው እንደ ተቋሙ ፍላጎት በጥቅል ወይም በተናጠል ሊለይ ይችላል፡፡
  15. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ በሙሉ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ከገዥው ተቋም ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  16. አሸናፊ ከሆነው ተጫራች ላይ 3 በመቶ ከተከፋይ ሂሳብ ግብር (With holding TAX) ተቀናሽ ይሆናል፡፡
  17. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውሉን መፈጸም ይኖረበታል፡፡ በተባለው ቀን መጥቶ ውሉን የማይፈፅም ከሆነ ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  19. ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመምጣት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡

የመካነ ኢየሱስ ገንዝብ አካባቢ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here