በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት በ2018 የበጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 አላቂና ቋሚ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት 4 ቋሚ አላቂ ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት 5 የቢሮ ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸር፣ ሎት 6 የመኪና ጎማ፣ ሎት 7 ብስክሌት የብስክሌት ጎማና ካላማዳሪ እና ሎት 8 የደንብ ልብስ ጥቅል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣታፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ከነቫት ከጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶችን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን በህዳር 30/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ቢሆን በቀጣዩ ባለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ የህግ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ስለሆነ ከሎቱ የተዘረዘሩት እቃዎች በሙሉ መሞላት አለባቸው፡፡
- በሎት ከተዘረዘሩት እቃዎች አንዱን እቃ ሳይሞሉ የቀሩ ተወዳዳሪዎች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 01 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ፍትህ እና የህግ ኢንስቲትዩት
ባሕር ዳር

