በደቡብ ጎንደር አስተዳዳር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ ሎት 4 አርኒቸር እና ሎት 5 የመኪና ጐማ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች፡-
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ክፒ ከመጫሪቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ይህ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ በፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት ከዋናው ጋር ሊገናዘብ የሚችልና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማስረጃ በማቅረብ እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ 30.00 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በባንክ ያስያዙትን ገንዘብ /ሲፒኦ/ ወይም /ጥሬ ገንዘብ/ ከመ/ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ አሽገው ፋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ብለው በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 5 እስከ 16ኛው ከቀኑ 3፡30 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን የሚታሸገውም በዚሁ ሰዓት ነው፡፡
ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት /ባይገኙም/ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ 16ኛው ቀን በ 3፡45 ይከፈታል፡፡
የጨረታ መከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
የጨረታ አሸናፊው የሚሆነው በጥቅል /በሎት/ ነው፡፡
የሚገዙ ዕቃዎች ርክክቡ የሚፈፀመው በሙያተኛ ተረጋግጦ ነው፡፡
አቅርቦቱ ደቡብ ጎንደር ዞን ደ/ታቦር ከተማ ፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ይሆናል፡፡፡
የሚገዙትን ዕቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ በስልክ ቁጥር 058 441 30 36 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት