ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
73

በሰሜን ጎጃም ዞን የይልማና ዴንሳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለይልማና ዴንሳ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ  ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የይ/ደወ/ትምህርት ጽ/ቤት የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማለትም ሎት 1 ኮቲ ቀበሌ፣ ሎት 2 አንጋር፣ ሎት 3 ትሎማ እና ሎት 4 አይባር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ተጫራች መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የቲን ተመዝጋቢ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በዘርፉ አግባብነት ያለዉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የኤሌክትሮኒክስ ግዥው ከብር 200‚000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው ለግንባታዎች ከደረጃ 10 እና በላይ ያሉ የህንጻ ተቋራጮችን መሆን አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ሂሳብ ኤሌክትሮኒክስ 30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር/ እና የግንባታዎች 32,500/ ሰላሳ ሁለት ሽህ አምስት መቶ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከዋና ገንዘብ ያዥ አስይዘዉ ለግዥ ኦፊሰሮች ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል ወይም በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ከሆነ ከፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ማሸግ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ካለ ከአሸናፊዉ ዋጋ ጋር ተደምሮ ሲያዝ የተሸነፈዉ ተጫራች የሚያስይዘዉ ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡
  6. ጨረታዉ የሚከፈትበት ዕለት በበዓል ቀናት ከሆነ ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
  7. የኤሌክትሮኒክስ ጨረታ ሰነዱን ከህዳር 15/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት እና የግንባታዎች ጨረታ ሰነዱን ከህዳር 15/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 05/2018 ለ21 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ የሚቆይ ሲሆን የተሞላበትን ፎርም ቲን፣ የንግድ ፈቃድዎንና ሌሎች ያልተጠቀሱ ማስረጃዎችን በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. የኤሌክትሮኒክስ ጨረታዉ የሚዘጋበት ህዳር 30/2018 ዓ.ም በ3፡30 ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተዉ በዚሁ ቀን ህዳር 30/2018 ዓ.ም በ4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ፍላጎት ያላቸዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እንዲሁም የግንባታዎች ጨረታዉ የሚዘጋበት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም በ3፡30 ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተዉ በዚያው ቀን ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም በ4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ፍላጎት ያላቸዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በጨረታዉ መክፈቻ ዕለት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታዉን ለመክፈት የሚገድበዉ የለም፡፡
  10. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መያዝ አለበት፡፡
  11. ተጫራቾች አሸገዉ ከሚያስገቡት ሰነድ እና ፖስታ ላይ አድራሻና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  12. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  13. ጨረታዉን የምናወዳድረዉ በሎት (በጠቅላላ) ዋጋ ነዉ፡፡
  14. ግዥ ፈጻሚ አካል ያሸነፈውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  17. ጨረታዉ ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  18. የኤሌክትሮኒክስ ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ነዉ፡፡
  19. የግንባታ ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ ነዉ፡፡
  20. በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸዉ የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም በስልክ ቁጥር 0583380298 ማግኘት ይችላሉ፡፡

የይልማና ዴንሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here