የደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም የተለያዩ የማሰልጠኛ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ እቃዎች ማለትም ሎት 1 የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 2 የጽህፈት ማቴሪያሎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ሎት 4 የግብርና እቃዎች ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት6 አሌክትሪክ፣ ሎት 7 ኮፒውተርና የአይቲ ማቴሪያሎች፣ ሎት 8 የአውቶ እቃዎች፣ ሎት 9. ፈርኒቸር፣ ሎት 10 የጋርመንት እቃዎች፣ ሎት 11 የተዘጋጀ የደንብ ልብስ እና ሎት 12 ብትን የደንብ ልብስ ጨርቅ ሲሆኑ ሁሉም ውድድሮች በሎት ሲሆኑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ማስረጃውን አያይዛችሁ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጂ ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዱዱ የጨረታ አይነት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈልና በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን በ16ኛው ቀን 5፡00 ታሽጎ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም የመክፈቻ ጊዜው አይራዘምም በዚህ እለቱ በዓል ከሆነ በቀጣይ ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተወዳዳሪ ድርጅቱ ማህተም ስምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ደረቅ ቸክ ያስያዘ ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል፡፡
- ጨረታው ከብር 20,000 /ሀያ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ 3 በመቶ ይቀነስበታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸንፉትን እቃ ኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው እንደተገለፀላቸው በ5 ቀን ውስጥ ውል ከኮሌጁ ጋር መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የምንለየው በሎት ድምር የሚታይ ሰለሆነ ተጫራቾች ሁሉንም አይተሞች መሙላት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሁሉንም ማቴሪያሎች ያልሞሉ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ኮሌጁ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 117 08 06 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

