ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
63

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ ዋና መምሪያ የጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳድር ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2 የመኪና ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዉ ጋር ዉል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የሚገዛዉ የግዥ መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባችኋል፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የንግድ ፈቃድ ቲን ሰርተፊኬትና ቫት ሰርተፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ዉስጥ በማስገባት ወይም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ከህዳር 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱ ጓ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የማወዳደሪያ ስርዓቱ የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ነው፡፡
  6. የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር ለሎት 1 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ  በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ /መሂ 1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ጓ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት እለት ከህዳር 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ ህዳር 30/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት የመጫረቻ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በጓ/ወ ገንዘብ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ16ኛዉ ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛዉ ቀን ወይም የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈዉ ዉሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ በጓ/ወ/ገንዘብ/ጽ/ቤት በራሳቸዉ ወጪ በማምጣት በባለሙያና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች በማስፈተሸ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡ የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  11. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነዉ፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የንግድ ፈቃድ፣ ቲን፣ ቫት እንዲሁም የሚሞላቸው ሰነዶች ለሦስተኛ ወገን በግልጽ የሚታይና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ የግዥውን መጠን 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብት አለው፡፡
  14. ተጫራቾች በግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 225 05 06 /058 225 00 09 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጓንጓ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here