ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
66

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ኮፒውተር ፕሪተር ላፕቶፕ፣ ሎት 3  ተገጣጣሚ እቃዎች ማለትም ወንበር ጠረጼዛ ሸልፍ እና  ሎት 4 የጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በየዘርፍ የዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክሲ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና ናሙና የሚያስፈልጋቸው ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ዘወትር በስራ ስዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉዱ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በተናጠል በየሎት ምድባቸው የሚለይ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፋያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. በጨረታ 1ኛ የወጣውን ውል እስከሚወስድ ድረስ 2ኛ የወጣው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስም፡፡
  11. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሥዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ህዳር 15/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛት ይችላል፡፡
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን ህዳር 30/2018 ዓ.ም በተዘጋጀው ሳጥን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አያግደውም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ለአ/ጊስ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣት በባለሙያና በጥራት ኮሚቴው ስለእቃው ጥራት በማስፈተሸ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
  17. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 118 08 46 /09 35 28 46 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአምባጊዮርስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here