ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
95

የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል አድራሻ ባሕር ዳር አባይ ማዶ ቀበሌ ህዳር 11 ከኮበል ኢንዱስትሪ ጎን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች ሎት 1 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የብስክሌት መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 5 የህንፃ መሳሪያዎች፣ ሎት 6 የህክምና እቃዎች፣ ሎት 7 ብረታ ብረት፣ ሎት 8 ብትን ጨርቅ፣ ሎት 9 ጫማዎች፣ ሎት 10 ሸሚዝ፣ ሎት 11 ስፊት፣ ሎት 12 የኬን ገመድ እና ሎት 13 ሴንቴቲክ ሌዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  3. ተጫራቾች የዋጋዉን ጠቅላላ አንድ በመቶ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ዋጋቸዉ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር / በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
  5. ማዕከሉ ከሚገዛዉ ዕቃ የዋጋዉን 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለዉ፡፡
  6. አሸናፊዉ ድርጅት የዉል ማስረከቢያ የዉሉን ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. አሸናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል ዋጋ በመሆኑ ሁሉንም የተዘረዘሩት ዕቃዎች መሙላት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  10. የእቃዎችን አይነት (ሞዴል) ማዕከሉ ድረስ በአካል መጥቶ ማየት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛዉ ቀን 3:30 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈዉን እቃ ከማዕከሉ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
  13. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ለወደፊትም ከመንግስት ግዥ እንደማይሳተፉና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያም የሚወረስ ይሆናል፡፡
  14. ማዕከሉ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 321 54 82 /058 820 97 84 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 5 ቀርቦ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የባሕር ዳር አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ አገልግሎት ማዕከል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here