በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ፍ/ቤት የግዥና /ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቡድን ለእናርጅ እናወጋ ወረዳ ፍርድ ቤት እና ለፈ/ብርሀን ን/ወ/ፍ/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽፈት መሳሪያ፣ ሎት2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 ፈርኒቸር/ የፋብሪካ ውጤት ሎት 5 ህትመት እና ሎት 6 አነስተኛ የእጅ መሳሪያ እንዲገዛላቸው በጠየቁት መሰረት ግዥውን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ጨረታው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሚገመቱ የጨረታ ሰነዶች (የቫት) ተመዝጋቢነት ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ሲመጡ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ግዥና/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቡድን ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በባንክ ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ-1 ገቢ አድርጎ የመሂ አንዱን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር (ሲፒኦ) ብሎ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን እና ፊርማቸውን በማስፈር በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሰነዱን ለማስገባት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ16 ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ጨረታው ይከፈታል፡፡ እለቱ የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ጨረታው ይከፈታል፡፡ አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ5 ተከታታየ ቀናት በኃላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት በመያዝ በአሸነፈበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ዋስትን በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጥ የባንክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ መቆያ ጊዜ በተመለከተ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 40 ተከታታይ ቀን ውስጥ ጸንቶ ይቆያል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው አቃውን ደብረ ወርቅ ከተማ ፍርድ ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 59 63 39 /09 22 71 53 31 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ፍ/ቤት

