በአብክመ ዋና ኦዲተር ደሴ ወኪል መ/ቤት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4. የፈርኒቸር እቃዎች እና ሎት 5. የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች ህጋዊ ተጫራቾችን በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- ማንኛዉም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፡፡
- ለዚህ የተዘጋጀውን ሠነድ ቢሮ ቁጥር 05 በአካል በመቅረብ በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሠነድ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ መሞላት ይኖርበታል፡፡
- የተሞላው ዋጋ ቫትን የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ መግለጽ ይኖርበታል፡፡ የተገለፀ ነገር ከሌለው (ከቫት) ጋር እንደተሞላ ይቆጠራል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዛቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከሠነድ ጋር አብሮ አያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ወጥቶ የሚቆይ ሆኖ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033 312 00 63 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአብክመ ዋና ኦዲተር ደሴ ወኪል መ/ቤት

