ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
68

በምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የደጋ ዳሞት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እና ሎት 2 ዲዝል ጀነሬተር በናፍጣ የሚሰራ ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ (ህጋዊ ሰርተፊኬት) ያወጡና የተሰጣቸዉ ፈቃድ አንድ ዓመት የሞላዉ ከሆነ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከብር000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ሲመጡ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘዉ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል  ከሆነ በቀጣዩ ቀን ሰዓቱን ሳይቀይር ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ደጋ ዳሞት ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  8. አሸናፊ የሆነዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ5 የቅሬታ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊ የሆነበትን እቃ ደጋዳሞት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማስረከብ አለበት፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ዋጋ ነው፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 10 53 48 14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደጋ ዳሞት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here