ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
142

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በባሕር ዳር ከተማ በትምህርት መምሪያ ሥር ላሉ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ቅድመ አንደኛ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ የሚሆን 200 ሚሊ ሊትር ፓስቸራይዝድ ወተት እና 100 ግራም ዳቦ እንዲቀርብላቸው በጠየቁት መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ስለሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚቀርበው ዳቦ እና ወተት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሺን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. አቅራቢው ተቋም በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ከምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የምግብ ጥራትና ደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. ለማጓጓዣ የሚጠቀምበት መኪና ኮልድ ቫን ማቀዝቀዣ የተገጠመለት አቧራ እና ፀሀይ መከላከያ ያለውና በተመረጡ ት/ቤቶች ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናል ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፅሁፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 46 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 46 በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 46 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 93 73 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here