በምሥራቅ ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ል/ት/መምሪያ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በመደበኛ በጀት ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የውሃ እቃ፣ ሎት 3 ስሚንቶ፣ ሎት 4 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 6 የዉጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 7 የሀገር ውስጥ ፈርንቸር እና ሎት 8 የእንስሳት መደሀኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ከላይ በተጠቀሱት በሥራ ዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎችን ማያያዝ እንዲሁም የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙት እቃዎች የእቃውን ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ብር ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ለእያንዳንዳቸው ሎት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 03 በመክፈል ከዋና ገ/ያዥ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሎት 1 ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ሎት 2 ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣ ሎት 3 ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/፣ ሎት 4 ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/፣ ሎት 5 ብር 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/፣ ሎት 6 ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ ሎት 7 ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ እንዲሁም ሎት 8 ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በኢትዮጵያ ብር በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጥቅል (ሎት) ስለሆነ ከተጠቀሱት እቃዎች ውስጥ አንዱንም ያልሞላ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተኛው ቀን 11፡30 ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በደ/ጥላ/ማ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ክፍል ለዚሁ ለተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን በሥራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት 1 እስከ ሎት 8 በ16 ተኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሎት 1 እስከ ሎት 8 በደ/ጥ/ግን/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ16 ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ጀምሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ጠቅላላ እቃዎች ከደባይ ጥላት ግን ወ/ረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሥር ባሉ ንብረት ክፍሎች ድረስ በመምጣት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ (በሲፒኦ) ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ወይም ድርጅት ለመንገዱ የሚያስፈልጉ ማቴሪያል ወይም ቁሳቁስ ትራንስፖርት በተመለከተ ቦታው ድረስ ራሱ የሚያጓጉዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 058 257 02 57 /01 43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

