ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
78

የእብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለእብናት ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ለ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ሎት 1 ከእብናት እስከ እባጭኮ ቀበሌ 20 ኪ/ሜ እና ከእብናት እስከ ዋሪባ ቀበሌ 20.4 ኪ/ሜ በአጠቃለይ 40.4 ኪሜ የመንገድ ጥገና ሥራ እና ከመጨና ጉናጉና ቀበሌ 10.2 ኪ/ሜ የመንገድ ቆረጣ እና ድልዳሎ ሥራ ለማስራት ስለተፈለገ የተለያዩ የማሽን ኪራይ እና ሎት 2 ለእብናት  ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚዉል በህብረት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት G+1 ባለ 10 የመማሪያ ክፍል ግንባታ ለማስገንባት ፈልጋል፡፡ በጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ ሆኑ፡፡
  4. የማሽኖች የባለቤትነት ሊብሬ እና ኢንሹራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ለትምህርት ቤት ግንባታ ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
  6. ለት/ቤቱ ግንባታ ተወዳዳሪ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ወረዳ ዝንበብ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ እብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን የግቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ ኦርጅናል ሰነድ አብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር በድን ቢሮ ቁጥር 06 ባዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ ለ21 ቀን ቆይቶ በ22ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ጨረታው በወጣ በ22 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ (የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው ለሥራ በተፈለገበት ሰዓት ለ3 ቀናት ተጠብቆ ካልቀረበ በመመሪያ መሰረት መብቱ እርምጃ መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር በሚሞሉበት ሰዓት ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
  12. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 06 የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  13. ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  14. አሸናፊ የሚለየዉ በጥቅል ደምሮ ይሆናል፡፡
  15. አሸናፈው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  17. ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 20 ቀን ይሆናል፡፡
  18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 440 06 06 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here