የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መ/ቤት ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የኦዲት ጨረታና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ህጋዊና ብቃት ካላቸው በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ሎት 1 የ2017 በጀት አመት የዉጭ የኦዲት አገልግሎት፣ ሎት 2 የመኪና እቃዎች፣ ሎት 3 የመኪና ታፕሰሪ፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ ከነ ስፌቱ፣ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች እንዲሁም ሎት 6 ሸሚዝና ተዛማጅ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መ/ቤት አድራሻ ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ባ/ዳር ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት በተከራየዉ G+3 ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 304 በመምጣት የኦዲት ጨረታዉን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ እና ሌሎች ጨረታዎችን ደግሞ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን (ቫትን) ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት ንብረቱን የሚረከበው በተጠቃሚዎች የጥራት ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
- አሸናፊው ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ የዉል አፈጻጸም ዋስትና (ፐርፎርማንስ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱም ሆነ ከተጠየቀዉ (ስፔስፊኬሽን) ዉጭ ምንም አይነት ፅሁፍ ማስፈር የለባቸውም፡፡
- ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 201 ከረፋዱ 4፡15 በግልጽ ይከፈታል፡፡ በ22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 00 86 23 30 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅ

