ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
50

በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የአዲስ አለም ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽዳት አውት ሶርስ አገልግሎት፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች አቅርቦት፣ ሎት 3 የጥበቃ አውት ሶርስ አገልግሎት፣ ሎት 4 የተለያዩ የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 5 የደንብ ልብስ አቅርቦት እንዲሁም ሎት 6 ኪችን ካብኔት ሥራዎች አቅርቦት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ፡-

  • በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  • ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የጽዳት አውት ሶርስ እና የጥበቃ አውት ሶርስ ከመንግስት መ/ቤት ወይም ህጋዊ የግል ድርጅት ተቋማት ከሁለት ተቋማት የአንድ አንድ አመት የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የግል ድርጅት የሥራ ልምድ የሚቀርብ ከሆነ የሥራ ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በዚህ ያልተጠቀሱ የጨረታ መስፈርቶች ከጨረታ ሰነዱ ላይ በተጨማሪ የሚቀርቡትን የመገምግሚያ ነጥቦች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ሰነድ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • 5ቱም በሎት የወጡት የጨረታ አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን 3፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  • አሸናፊ ማሸነፉን ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን 10 በመቶ የውል ማስያዣ ያስይዛል፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በታሸገ ፖስታ በአዲስ ዓለም ሆስፒታል ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 218 10 34 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አዲስ ዓለም ሆስፒታል

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here