ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
39

የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 በጀት አመት ሁለተኛ ዙር የወጣ ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የህንጻ መሳሪያ፣ ሎት 2 ብረታ ብረት፣ ሎት 3 ኤሌክትሪክ፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት 5 ኤምዲኤፍ እና የኮርኔስ ፕላስቲክ፣ ሎት 6 አውቶ፣ ሎት 7 ጽዳት እቃ ፣ ሎት 8 ቴክስታይል ጋርመንት ፣ ሎት 9 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 10 አገልግሎት ግዥ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ (ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር (ቲን) የተሰጣቸው እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የሚገዙት ዕቃዎች በተጠየቀው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኪሽን) መሰረት ሆኖ የጨረታ ሰነዱን እንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማግኝት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በመሂ 1 ወይም በባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳብ ማቅረቢያ ቅጹን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸና ፖስታ ከግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ሰነዱን በመግዛት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም በተደረገው የጨረታ አከፋፈት ሥርዓት ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  9. ኮሌጁ በጨረታው አሸናፊ ላይ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  11. የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት (በጥቅል) ወይም እንዳስፈላጊነቱ በተናጠል ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
  12. አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በሙሉ በራሱ ወጭ ኮሌጁ ግቢ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  1. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 02 00 በመደወል መረጃ ማግኝት  ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here