ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
53

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለዘር የማይዉል ሰብሎችና የተለያዩ ብጣሪዎችን ለመሸጥ በባሕር ዳር ዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ግቢ ዉስጥ ለሚገነቡ የብጣሪ ማከማቻ ማጋዘንና የመኪና ሸድ እና በእንጅባራ ዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ጣቢያ ዉስጥ የብጣሪ ማከማቻ መጋዘን ለማስገንባት፣ የመኪና እና የትራክተር መለዋወጫዎች፣ ዘይትና ቅባት የተለያዩ ጎማዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የፈርኒቸር እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ለመግዛት፣ የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች ፕሪንተሮችና ኮፒዎች ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፣ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስና፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (ቲን) ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መሥሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ለግንባታዉ የሚጠይቀዉ የሥራ ፈቃድ ደረጃ ሰባት እና ከዚያ በላይ ነዉ የሙያ ብቃት ማስረጃና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላቸዉ፡፡
  5. ከቆርቆሮ ዉጭ ሌላዉን ማቴሪያልና የሰዉ ሀይል አቅርቦ ሊሰራ የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት ባሕር ዳር ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሸጋገራል፡፡
  8. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  9. የተለያዩ ንፁህ ዘሮችና የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፡፡
  10. ግዥዉን በተመለከተ ባሕር ዳር ዋናዉ መሥሪያ ቤት መጋዘን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15 /09 18 01 69 35 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here