ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
52

በምሥራቅ ጐጃም ዞን የስናን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለባለበጀት ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1. የጽ/መሳሪያዎች፣ ሎት 2. ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 3. የመኪና ጎማ፣ ሎት 4. የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣ ሎት 5. ህትመት እና ሎት 6. የጽዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)  ምዝገባ ያላቸው፡፡
  3. ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሆኑ ግዥዎች (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎችን መጠንና ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሎት  ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ስናን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ የግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢንድ ቦንድ) ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1. ብር 8,000፣ ለሎት 2. ብር 10,000 ፣ለሎት 3. ብር 3,000፣ ለሎት 4. ብር 10,000፣ ለሎት 5. ብር 2,000 እና ለሎት 6. ብር 2,000  በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅ ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙበትን (ሲፒኦ) ወይም ደረሰኝ በተለየዩ ሶስት ፖስታዎች አሽገው ሶስቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ የመ/ቤቱን እና የአቅራቢውን ስምና አድራሻ በመጻፍ በማህተምና ፊርማ አስደግፎ ስናን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በሥራ ሰዓትና ቀን ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. የጨረታ  ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ባሉት ተከታታይ  ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ በማስገባት በዚህ ቀን ጨረታው ላይ ለመገኘት ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ቢሮ ቁጥር 04 ከጠዋቱ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊው የአሸነፉባቸውን እቃዎች ስናን ወረዳ በግዥ  ጠያቂ መ/ቤቶች ንብረት ክፍል አምጥቶ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 288 01 22 /128 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. መ/ቤቱ የሚያወዳድረው በሎት ነው፡፡
  14. በርክክብ ወቅት ለተጠቃሚው መሥሪያ ቤት ጥራታቸውን ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡

ማሣሠቢያ፡-

  • የጨረታ መክፈቻ ቀን የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ስዓት ይከፈታል
  • አድራሻችን ከደ/ማርቆስ ከተማ በ27 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንገኛለን፡፡

የስናን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here