ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
33

በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ቤት የፍኖተ ሰላም ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 መደበኛ በጀት ዓመት ለፍርድ ቤታችን አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ አወዳድሮ ግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
  4. በተራ ቁጥር 1-3 ላይ የተጠቀሱትን ኮፒዎችን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ፍኖተ ሰላም ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የግ/ፋን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታዉ የሚከፈተዉ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ከ15 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ16ኛ ቀን ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም 3፡00 ላይ ታሽጎ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸዉ በሚገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ባይገኙም ጨረታዉን ከመክፍት አያስተጓጉልም፡፡ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ቢሆን በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. የሚቀርበዉ ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀና መ/ቤቱ ከሚፈልገው ጥራት በታች ከሆነ መ/ቤቱ የማይቀበልና በሚደርሰው ኪሳራ ተጠያቂ የማይሆን መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡
  8. በዚህ ማስታወቂያ ያልተጠቀሰ ቢኖር በግዥ መመሪያዉ የምንገዛ ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ነው፡፡
  10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. ለበለጠ መረጃ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 78 73 37 /09 11 58 08 78 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የፍኖተ ሰላም ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here