ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
34

የግዥ መለያ ቁጥር 14/2018 ዓ/ም

ሱታና ንግድና የማማክር ሥራዎች ኢተርፕራይዝ ለፋብሪካ ግንባታ አግልግሎት የሚውሉ አሸዋ፣ ጠጠር 02፣ የተፈለጠ ድንጋይ፣ ለተማሪዎች ቀለብ የሚውል ቀይ ሽንኩርትና ድንች እንዲሁም የመኪኖች ጅፒኤስ ግዥ እና የጅፒኤስ ኢንስታሌሽን ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

  1. በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ሱታና ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢተርፕራይዝ ነዉ፡፡
  2. በጨረታዉ መወዳደር የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሱታና ንግድና የማማክር ሥራዎች ኢተርፕረይዝ ሥራ ክፍል የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መዉሰድና ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ /ፖስታ/ የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ ፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ኢተርፕራይዙ ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 203 የምትጫረቱትን የአንዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ የሚገዛዉ ዕቃ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ የሚሆን ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የግንባታ ቁሳቁስ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ የጂፒኤስ ብር 50,000 /ሀምሳ ሽህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. የጨረታዉ አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፋቸዉ ውል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ16 ተኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያዉ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  9. አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7 ቀን በኃላ ባሉት 8 ቀናት ዉስጥ ዉል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  10. ኢተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. አሸናፊዉ ድርጅት በግዥ መመሪያው መሰረት የቅድመ ግብር 3 በመቶ እንደሚቆረጥበት ታሳቢ ተደርጎ ዋጋውን መሙላት አለበት፡፡
  12. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 42 26 44 ደዉለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here