ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
63

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት የሃይሉክስ ሪቦ መኪና ኬሪቦይ እቃ እና ዓመታዊ የተለያዩ ህትመቶች ለማሣተም ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ወይም ፍሉድ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የሃይሉክስ ሪቦ መኪና ኬሪቦይ እቃ ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ዓመታዊ የተለያዩ ህትመቶች ብር 6,000 /ስድስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት ክፍል የገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በማድረግ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማለትም ከህዳር 22/2018 እስከ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፍትህ ቢሮ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በ16 ተኛው ቀን   ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. በሚገዙ የዕቃዎች (አገልግሎቶች) ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ፍትህ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here