ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
54

የጣቁሳ ወረዳ ፍርድ ቤት በመደበኛ በጀት በሎት ጠቅላላ ድምር ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸዉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀዉ በአማረኛ ቋንቋ ነዉ፡፡
  5. የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  7. የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  8. በጨረታ ሰነድ ላይ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ የሌለዉ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት በሰም የታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ፡፡ ነገር ግን በሰም የታሸገ ቢሆን ይመረጣል ባለመታሸጉ ጨረታዉ ወድቅ አይደረገም፡፡
  10. ጨረታዉ የሚቆየዉ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሁልጊዜ በሥራ ቀናት እስከ 11:30 ሰነዱ ይሸጣል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊ ግለሰብ ወይም ድርጅት እቃዉን ገቢ የሚያደርገዉ ጣቁሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ንብረት ክፍል ይሆናል፡፡
  12. ጨረታዉ የሚከፈተዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በይፋ የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመክፈቻዉ ቀን በአል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የዕቃዉ አይነት ዝርዝር መገስጫ (ስፔስፊኬስሽን)ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ጣቁሳ ወረዳ ፍርድ ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመስስ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነዉ፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 77 54 08 /09 23 39 71 33 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፦ የጨረታ ሰነዱ የሚገባዉ ጣቁሳ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በሚገኘዉ ሳጥን ዉስጥ ነዉ፡፡

የጣቁሳ ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here