ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለኮርፖሬሽኑ ለሥራ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን ማለትም ሎት 1.የጽህፈትና ጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 2 የመኪና ዲኮር ዕቃዎች እንዲሁም ሎት 3 የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ናሙና (ሳምፕል) ደግሞ ኮርፖሬሽኑ ያቀርባል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከኮርፖሬሽኑ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ገንዘብ ያዥ ክፍል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መ/ቤቱ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአረጋዊያን ህንጻ ከሚገኘዉ ኮርፖሬሽኑ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ውስጥ ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ የካሌንደር ቀናት ዉስጥ እስከ 11፡30 ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በ21ኛዉ ቀን ወይም በመዝጊያዉ ቀን የጨረታ ሰነድ አይሸጥም፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት አስከ 21ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ሲኖርባቸዉ 21ኛዉ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ግ/ፋ/ንብ/ አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 09 ዉስጥ በ21ኛዉ ቀን 4፡00 ይታሸግና በዚያዉ ዕለት 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም 21ኛዉ ቀን   እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይታሸግና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታዉ አሸናፊ የሚለየዉ በነጠላ ዋጋ ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊዉ ድርጅት ዕቃዎችን ባሕር ዳር ኮርፖሬሽኑ ቢሮ ድረስ በማምጣት ማስፈተሸ (በባለሙያ ማሳየት) አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ በኮርፖሬሽኑ የግዥ መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አብክመ ኢፓልኮ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 47 67 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here