ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የበየዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ለተቋሙ ለተለያዩ አገልግሎቶች ሊውል የሚችሉ ማለትም ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 የጽፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት 4 የፅዳር እቃዎች፣ ሎት 5 የቋሚ አላቂ እቃዎች እና ሎት 6 የተለያዩ ፈርኒቸር እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶችና በዘርፉ ከተሰማራችሁ ነጋዴዎች መካከል ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡

ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ጨረታው ከወጣበት ቀን 02/03/2017 ዓ.ም እስከ 15/03/2017 ዓ.ም በተከታታ ለ15 ቀናት በየዳ ወረዳ ፍርድ ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ 20.00 /ሃይ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የእቃ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም 02/03/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ላይ ይዘጋል /ይታሸጋል/፡፡ ሆኖም ግን የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ቅዳሜ /ካላደር/ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋል /ይታሸጋል/፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ቢገኝም ባይገኝም በበየዳ ወረዳ ፍርድ ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 8 በግልጽ ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን አድራሻ፣ ህጋዊ ማህተም፣ ሙሉ ስምና ፊርማ በመፃፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ መጠን የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በመ/ቤቱ መ/ሂ1 ማስያዝ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን አድራሻ፣ ህጋዊ ማህተም፣ የግብር መለያ ቁጥር፣ የንግድ ፈቃዱን እና የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ ከላይ በተራ ቁጥር 5 እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ከፖስታው ላይ ኮፒ እና ኦርጅናል በማለት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታው አሸናፊነት ድርጅት የአሸናፊ ውጤት ከተገለፅበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡

የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ / በመ/ቤቱ መ/ሂ1 በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን እቃ /ንብረት/ ለማቅረብ በጨረታ ሰነዱ /በደብዳቤ/ የተሰጠውን ሞዴል እና ዓይነት እንዲሁም ስፔስፊኬሽን ላይ ለውጥ ወይም ሳይቀይር ጥራቱን የጠበቀ እቃ ማቅረብ አለበት፡፡

አሸናፊው ድርጅት ያሸነፉትን እቃ /ንብረት/ በበየዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ንብረት መጋዝን ድረስ በማቅረብ የጥራት ኮሚቴው የንብረቱን ጥራት በማስፈተሽ የተሰጠውው ሞዴል እና ዓይነት እንዲሁም ስፔስፊኬሽን ሳይለውጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው የሚካሄደው በሎት /በምድብ/ ነው፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በአካል በበየዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 55 65  /09 24 26 87 97 በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡

የበየዳ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here