በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳዳር በ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ጎንደር ከተማ አባጃሌ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 ላይ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳሩበት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የገንዘብ መጠን አንድ በመቶ እና ከዚያ በላይ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በጥሬ ገንዘብ በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ስም በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሽገዉ ጎንደር ከተማ አባጃሌ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ጨረታውን እስከ 16 ተኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎንደር ከተማ አባጃሌ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 ላይ በ16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4፡00 ታሽጉ በዚሁ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- የእቃ ርክክብ ቦታ የሚደረገው ማእከላዊ ጎንደር ዞን ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መካዘን ድረስ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጎንደር ከተማ አባጃሌ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 00 41 59 24 በመደወል ማግኘት መረጃ ይችላሉ፡፡
የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጸ/ቤት

