የደንበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማዉ ዉስጥ ለሚገኙ ባለ በጀት መ/ቤቶች የ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እና ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጽህፈት መሳሪያ ሆነ የኤሌክትሪክ እቃዎች አቅርቦት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም ደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ደረሰኝ በመክፈል ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ስለ ትክከለኛነቱ በማህተም በማረጋገጥ ከጨረታዉ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መገለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደምበጫ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚዉል ይሆናል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋጋዉን በመሙላት የጨረታ ሰነዱን ገልፆ በመፃፍ ንግድ ፈቃድ፣ቲን ነምበር፣ የቫት ተመዝጋቢ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ በማድረግ በፖስታዉ ላይ የድርጅቱ ማህተም ስም ፊርማ፣ አድራሻ በማስቀመጥ ለደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ16 ተኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጉ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎችቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በተራ ቁጥር ቁጥር 10 የተጠቀሰዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ጨረታው 16 ተኛዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀ የእቃ ዝርዝር (ስፔስፊክሽን) ዉጪ ላይ መጥቀስ አይቻልም፡፡
- አሸናፊዉ ተጫራች አሸናፊነቱን ከተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ደምበጫ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ዉል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
- የግዥ አቅርቦቱን አሸናፊዉ ዉል በያዘ 10 ቀናት ዉስጥ እቃዉን በራሱ ትራንስፖርት በማጓጓዝ እና በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ደምበጫ ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊዉን አገልግሎት በጥቅል ዋጋ በማወዳደር አሸናፊዉን የሚለይ ይሆናል፡፡
- ግብርና ታክስ የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ቅድሚያ ክፍያ ጽ/ቤቱ የማይከፍል መሆኑን ይታወቅ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሙሉ በሙሉ የመሙላት ግዴታ አለባቸዉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታዉን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደምበጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 773 02 81 /058 773 02 83 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደምበጫ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

