በአብክመ የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለተቋማችን አገልግሎት የሚዉሉ ልዩ ልዩ አቅርቦቶችን ማለትም ሎት 1 የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ዘመናዊ ካሜራ እና ሌሎች)፣ ሎት 3 የህክምና መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት 6 የዉሃ ዕቃዎች እና ሎት 7 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መሰፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ተከታታይ ደረሰኝ ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች በዘርፉ የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የአቅርቦቶቹን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግቢ ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 3፡35 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ እንደ በጀቱ መጠን 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብት አለዉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች የዋጋ መሙያ ጨረታ ሰነዱን በየሎት ምድቡ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለህክምና መሳሪያዎች ብር 250,000፣ ለፈርኒቸር ዕቃዎች አቅርቦት ብር 100,000፣ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 80,000፣ ለጽዳት ዕቃዎች ብር 25,000፣ ለተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ፣ ለዉሃ ዕቃዎች እና ለኤሌክትሪክ ዕቃዎች ለእያንዳንዳቸዉ ብር 10,000 መጠን ያለዉ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች የሚለየው በየ ሎቱ ምድቡ በድምር ዋጋ ይሆናል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን የበዓል ወይም የሥራ ዝግ ቀን ቢሆን ጨረታዉ በሚቀጥለዉ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 38 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ኢንስትትዩቱ የሚሰበስበው 3% ዊዝሆልድ ብቻ ነዉ፡፡
የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

