የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር መንገድ መምሪያ ለማሽነሪ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የማሽነሪና የከባድ መኪና ጎማ እና ሎት 2 የማሽነሪና የከባድ መኪና የመለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዛው የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ስለሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን እና የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ መሂ 1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 22/2018 አስከ ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የማወዳደሪያ ሥርዓቱ በየሎት በጥቅል ዋጋ ነው፡፡
- የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በግ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 22/2018 አስከ ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዊ ብሄ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ይደረጋል፡፡ ተጫራቾች ተገኙም አልተገኙም በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- የሚሞላዉ ዋጋ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር (ታክስ) የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ወጭዎች ማካተት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ አዊ ብሔ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያ በማስፈተሽ የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 227 00 66 /09 13 57 28 63 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

