ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
46

በደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን በአቀስታ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ የ2018 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት እቃ፣ ሎት 2 ፈርኒቸር፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 የቢሮ ቋሚ አላቂ እቃዎች ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡በመሆኑም በዚህ ዘርፍ ንግድ ፈቃድ ያለቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ያቀርባሉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ሽያጩ ከብር 200,000 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና አስፈላጊ ማስረጃዎች ጥርት ያለ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ውድድሩ የሚካሂደው በሎት ወይም በድምር አሸናፊ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ወይም (ቢድ ቦንድ) ከ60 ቀን ያልበለጠው የሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ የሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ እና ፋይናንስ የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን 11፡20 ድረስ ማስገባት ይቻላል እና በዚሁ ቀን 11፡30 ይታሸግና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻዉ በተገኙበት የመክፈቻ ቀን በቀጣይ ማለትም በ16ኛው ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡
  6. ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
  7. የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ማካተተ አለበት፡፡ የቫት ተወደዳደሪ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለበት፡፡
  8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች በፖስታው ላይ ቀን፣ ስም፣ ፊርማ፣ ስልክ መጻፍ አለባቸው፡፡
  10. ከላይ ከተረዘሩት እና በተጨማሪ ሁሉም ተጫራች የግዥ መመሪያውን እስከ ማሻሻያወቹ ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ይውላል፡፡
  13. መ/ቤቱ በያንዳንዱ ግዥ ላይ 20 በመቶ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥራችን 09 14 34 01 36 /09 22 61 68 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአቀስታ ከተማ አሰተዳድር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here