የግዥ መለያ ቁጥር አብክመ/ኢቴቢ/ግ/ጨ/ 03 /2018
በአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የፅህፈት እቃዎች ፣ሎት2. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት3. የICT እና ኢንተርኔት፣ ሎት4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት5. የፎቶና ቪዴዮ ካሜራ፣ ሎት6. የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት7. የብስክሌት መለዋወጫ፣ ሎት8.የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ሎት9. የተሽከርካሪ ዲኮር እቃዎች፣ ሎት10. የኤሌክትሪክ እቃዎች ፣ሎት11. የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት12. የውሃ መስመር መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት13. የደንብ ልብስ አልባሳት፣ ሎት14.የህፃናት መገልገያ እቃዎችን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ዋጋ የሞሉበት እያንዳንዱ ቅፅ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ. 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውንማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 00 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች ግዥ የሚፈፀምላቸውን እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ሎት (ግዥ) ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ጨረታው በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 8፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በቢሮው ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል (በሎት) ዋጋ ይሆናል፡፡
- በአንድ ሎት ላይ በከፊል ዋጋ ሞልቶ መወዳደር ከዋጋ ውድድር ውጪ ያደርጋል ፡፡
- በዋጋ መሙያ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል አለማድረግ ከውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ

