በምሥራቅ ጐጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት አመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎችን፣ አንዲሁም ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘውትር በሥራ ስዓት እነማይ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ንብ/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ገንዘቡን በመ/ቤታችን መሂ 1 ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ (ስፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚውል ሲሆን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ይታሸግና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆነ ነገር መኖር የለበትም በጨረታ ሰነዱ እና በፖስተው ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
- በባለሙያ የሚያረጋግጡ እቃዎቹን በባለሙያ እያረጋገጥን የምንረከብ መሆኑና አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸው እቃዎችን በእነ/ወ/ፍ/ቤት ሥር ባለው ንብረት ክፍል ድረስ አስፈላጊውን ወጪ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- በእያንዳንዱ ሎት መ/ቤቱ አሸናፊ የሚለየው ጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች በየምድቡ የቀረቡትን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፡፡
- ከሎት 1-4 ላሉ የሎት ምድቦች ጽ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታ ይዘት ሳይቀየር ሥራው ከጠቅላላ መጠን ላይ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 01 46 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእነማይ ወረዳ ፍ/ቤት

