በደቡብ ጎንደር ዞን የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገ/ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት አቅርቦቶችን ማለትም. የውሃ መገጣጠሚያ እቃዎች እና የውሃ ቆጣሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለቸው፡፡
- የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፈኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከገ/ግ//ፋ/ን/አስ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲ.ፒ.ኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጂዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለመካነ ኢየሱስ ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ቀን 11፡00 ጨረታው ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 8 በ16ተኛው ቀን 4፡00 ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 447 03 02/ 09 18 18 84 82 /09 46 12 49 45 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡