ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
136

በሰሜን ጐጃም አስተዳደር ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት በወረዳው ላሉ 1ኛ. የትምህርት ጽ/ቤት ወተት አባይና ባችማ ቀበሌ አንድ አንድ ብሎክ የመማሪያ ክፍል፣ 2ኛ.የጤና ጽ/ቤት ስር ፣3ኛ. በጤና ጽ/ቤት ስር ላሉ ለይነሳ ለምርት አጠቃላይ ጤናታጠቅ ለስራ አጠቃላይ ጤና ኬላ ለእድገት መሰረታዊ ጤና ኬላ እና ለአዲስ ልደት መሰረታዊ ጤና ኬላ እና ለአዲስ ልደት መሰረታዊ ጤና ኬላ ግንባታዎች፣4ኛ. በመንገድና ትራንስፖርት ፅ/ቤት ከቻይና ካምፕ አማሪት እና ከመርዓዊ ቆለላ የመንገድ ጥገና ማሽነሪ ኪራይ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግንባታዉን ማስገንባትና ማሽነሪዎችን ተከራይቶ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ያላቸው፡፡
  4. የግንባታው ተጫራቾች ደረጃ ስምንት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸዉ፡፡
  5. የግንባታ ተጫራቾች ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ሆነዉ የመልካም ስራ ፈፃጸም ማስረጃ  ማቅረብ  የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሞሉት ጥቅል ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-6 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን ) ከጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለግንባታዉ በ21 ተከታታይ ቀናት እና ለማሽነሪ ኪራይ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ በሰ/ሜ/ወ/ ገን/ጽ/ቤት በግዥ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 38 መግዛት ይችላሉ፤ ነገር ግን 22ኛው እና 16ኛዉ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት በሞሉት ዋጋ ብር አንድ በመቶ በባክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ( ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ያልተመሰረት የባንክ ዋሰትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰ/ሜ/ወ/ገን/ጽ/ቤት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 38 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ መጨረሻው የመዝጊያ ስዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. የጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስደም፡፡
  14. የግንባታው አሸናፊ ድርጅት የግንባታ ጠቅላላ ወጭዎችን ራሱ የሚሸፍን ሲሆን የማሽነሪ ኪራይ አሸናፊ ነዳጅና ቅባት የኦፕሬተር አበልና የሎቤድ ኪራይ አሸናፊዉ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  15. ተጫራቾች በዋጋ መሙያው ላይ ማህተምና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 38 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 330 04 32 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here