ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
107

ቁጥር 08/2018

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የጂም ዕቃዎችን  በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 ፣ብር 300 (ሶስት መቶ) ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡  ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥ ክፍል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ስፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉት ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ባሕር ዳር በሚገኘው ዋናው ቢሮ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here