ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
127

በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዳባት ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ ግንባታ ከተያዘው የካፒታል በጀት ለሚገነባው አስተዳደር የቢሮ ግንባታ በዳባት ከተማ ቀበሌ 04 በሚገኘው ቦታ ላይ በሙሉ ዋጋ በጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሙ ተጫራቾች ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡

  1. ህጋዊና የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የ2018 ዓ.ም የዘመኑን የንግድ ፈቃድ ያደሱ የ2017 ዓ.ም የታደሰው እስከ ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም የሚያገለግል ያሆናል፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱት የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 23 ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. የሚገዙትን የእቃ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም በመ/ቤቱ ዋና ገ/ያዥ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ እና (ሲፒኦ) ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ግዥ ቡድን ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና ከ2 በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን ዋና እና ኮፒውን በመለየት አጠቃሎ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 23 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  12. ጨረታው በጋዜጣ ወጥቶ የሚቆይበት ጊዜ ከህዳር 22/2018 እስከ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 23 በቀን ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  14. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
  15. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ  ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  16. የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ወይም  ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  17. ተጫራቾች ከመሀንዲስ ግምት 25 በመቶ በታች ከሞሉ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
  18. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ  አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው ዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 23 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 113 02 05 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  20. ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፈቃዳቸውን ሰነድ ለሚሸጡ ረዳት ገንዘብ ያዥ እያሳዩ መሆን አለባት፡፡ ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻ ለረዳት ገንዘብ ያዥ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here