በአብክመ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተሸከርካሪ ጥገና የአገልግሎት ግዥ እና የፎቶ ኮፒ፤የፕሪንተር እና የፋክስ ጥገና የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢነት ሰርቲፊኬት እና የሚገዙ እቃዎች ዋጋ ከ200 ሽህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርቲፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 እስከ 3 የተገለጹትን መስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚገዙ የተሸከርካሪ ጥገና የአገልግሎት ግዥ እና የፎቶ ኮፒ፤ፕሪንተር ፤ ፋክስ የአገአልግሎት ግዥ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾችየጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለተሸከርካሪ ጥገናዉ 5,000 /አምስት ሽህ ብር/ ፣ለፎቶ ኮፒ ለፕሪንተር እና ለፋክስ ጥገናዉ ደግሞ 1,000 /አንድ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በአል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ጨረታዉ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- የገዥ መ/ቤት አድራሻ አ.ብ.ክ.መ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባህር ዳር ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 058 218 00 14/ 058 218 11 03 ይደውሉ፡፡
የአብክመ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

