በምሥራቅ ጎጃም አስዳደር ዞን የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በወረዳችን ሥር ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ከ2018 የመደበኛ በጀት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ የውጭ ስሪት ፈርኒቸር፣ ጀነሬተር፣ የመኪና ጎማና ካለማዳሪያ፣ የውሃ ህክምና እቃ እና የህንፃ መሳሪያ በተጨማሪ ከመነሃሪያ በጀት የውጭ ስሪት ፈርኒቸር እና የኤሌክትሮኒክስ እቃ እንዲሁም ከስፖርት ምክርቤት በጀት የስፖርት ትጥቅ እና የስፖርት ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው በዘርፉ ከተሰማሩ ነጋዴዎች መካከል የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ጨረታው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በውድድሩ መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ የደ/ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ በአድራሻ ለደ/ኤ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ለኤሌክትሮኒክስ እቃ ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ ፣የመኪና መለዋወጫ እቃ ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/፣ የውጭ ስሪት ፈርኒቸር ብር 40,000 /አርባ ሽህ ብር/፣ የጀኔሪተር ብር 15,000 /አስራ አምስት ሽህ ብር/፣ የመኪና ጎማና ካለማዳሪያ ብር 5,000 /አምስት ሽህ ብር/፣ ለህንፃ መሳሪያ ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ የውሃ ህክምና እቃ ብር 2,000 /ሁለት ሽህ ብር/ በተጨማሪ ከመነሃሪያ በጀት የውጭ ስሪት ፈርኒቸር ብር 2,000/ ሁለት ሽህ ብር/ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃ ብር 2,000 /ሁለት ሽህ ብር/ እንዲሁም ለስፖርት ትጥቅ እና የስፖርት ጫማ ብር 5,000 /አምስት ሽህ ብር/ መ/ቤታችን መሂ 1 ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ይዘጋና በዕለቱ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የግዥ እና ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ አከፋፈት ስነ ስርዓት ላይ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀን ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡ ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ በመ/ቤቱ መሂ 1 ወይም በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በአድራሻ ለደ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና አድራሻ በመሙላት የታደሰ ንግድ ፈቃድና የቲን ምዝገባ፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት በማያያዝ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚከፈትበት 16 ተኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በተጫራቾች የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ለ30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚያስቀምጠው አይነት ወይም (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ሰነዳቸውን ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቹ የአሸነፈውን እቃ ደ/ኤልያስ ወረዳ ሥር በሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ውድድሩ በጥቅል ዋጋ ድምር ወይም በሎት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ሌሎች ያልተጠቀሱ አሰራሮች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 250 04 85 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

