የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች የ2018 በጀት አመት የሚጠቀምባቸው የአቅርቦት ግዥዎች ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ እቃ አቅርቦት ግዥ፣ሎት2. የኤሌክትሮኒክስ እቃ አቅርቦት ግዥ፣ ሎት3. የጽዳት (የንፅህና) እቃ አቅርቦት ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአቅርቦት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1. 15,000 /አስራ አምስት ሽህ ብር/ ሎት2. 10,000 /አስር ሽህ ብር/ እና ሎት3. 2,000 /ሁለት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እንዲሁም በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በደረሰኝ በማስያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ (ከዋጋ መሙያ) ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸው በተሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ ሲሆን ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ስርዝ ድልዝ ካለው ራሳቸው የሰረዙት ለመሆኑ ፓራፍ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዋጋውን በመሙላት የተጫራቹ ስም፣ ፊርማ፣ ማህተምና ሙሉ አድራሻ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ፣ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀትና ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎችን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ፖስታው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በተራ ቁጥር 8 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በአሸነፈበት የአቅርቦት ግዥ ውል በመፈፀም አቅርቦቱን መፈፀም ይጠበቅበታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በየሎቱ ጥቅል ድምር አሸናፊውን የሚለይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት 100 ( አንድ መቶ ብር ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደም/ዙ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስል ቁጥር 058 773 02 74 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

