በሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ የጠለምት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ/ን/ አስተዳደር ቡድን ለወረዳዉ ሴ/መ/ቤት መደበኛ በጀት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2 ደንብ ልብስ፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 4 የመኪና ጎማ እቃ ለ2017 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የእቃ ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ፡፡
ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ሂ 1 ቆርጦ አርጅናሉን ማስያዝ የሚችሉ፡፡
የሚገዙትን የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫዎች /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ መግኘት ይችላሉ፡፡
ሰነዱን ለመግዛት የምትፈልጉ ሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ/ን/ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3፣ ማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በላይ እና አገልግሎት ከግዥ ከ3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ በላይ ሁለት በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ ገቢ ይደረጋል፡፡
ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ጋዜጣዉ ታተሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥ/ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ይህ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ16 ተኛዉ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ/ን/ አስተዳደር ቡድን ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ይከፈታል፡፡ እንዲሁም በ17ኛዉ ቀን የሚከፈቱት ሎት 4 የመኪና ጎማ ከረፋዱ በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ/ን/ አስተዳደር ቡድን ይከፈታል፡፡
አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን እቃ የሚያቀርበው በራሱ ወጭ በባለሙያ እየተረጋገጠ በጠለምት ወረዳ ግዥ/ን/አስ/ ቡድን ንብረት ክፍል ገቢ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
መሥሪያ ቤቱ ይህንን ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጨረታ ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ ሎት ዋጋ ድምር ይሆናል፡፡
የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
ጨረታዉን ለማዛባት የሚሞክር ማንኛዉም ተጫራች ካሉ በክልሉ የግዥ አዋጅ 179/2003 ዓ.ም እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ከጨረታ ዉድድር ዉጭ ይደረጋሉ፡፡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዉርስ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በጨረታዉ ዉጤት ቅሬታ ካለ የጨረታዉ ዉጤት በማስታወቂያ ቦርድ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅሬታቸዉን ለጠለምት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በሥራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 28 97 /09 48 81 13 13 /09 18 04 22 25 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጠለምት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት