ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
27

የጃዊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ንብ/አስ/ቡድን ለጃዊ ወረዳ ሴ/መ ቤቶች ለ2018 በጀት አመት ለአገልግሎት የሚውሉ ሎት1. ብትን ጨርቅ ፣ሎት2. የተዘጋጀ የደንብ ልብስ፣ ሎት3. የስፖርት አልባሳት እና ቁሳቁስ ፣ሎት4. እስቴሽነሪ፣ ሎት5. የመኪና ጎማ፣ ሎት6. ኤሌክትሮኒክስ  በግልጽ  ጨረታ  አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፍዮች መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ግዥው ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ (ቫት) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን ፖስታዎች በማሸግ እና በሁሉም ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ሙሉ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር በማስፈር ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ዕቃውን በጃዊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዝን ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀበት ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ የውል ማሰከበሪያ 10 በመቶ ማሰያዝ አለበት፡፡
  7. በጨረታ ሰነዱ ሰንጠረዠ ላይ የተዘረዘሩትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት ነው፡፡
  9. የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮዽያ ብሄራዊ ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የዋጋውን አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
  11. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት1 እስከ ሎት6 ከህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታሕሳስ 13/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሠነዱን ጃዊ ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. የጨረታ ሰነዱ የሚመለሰው ታሕሳስ 14/2018 ዓ/ም ይሆናል፡፡
  13. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈተው ታሕሳስ 15/2018 ዓ/ም 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  14. የስራ ሂደቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝሩን (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታው ሠነዱ ላይ ያገኙታል፡፡
  16. የደንብ ልብስ እና የስፖርት አልባሳት ክልሉ ባወጣው መመሪያ መሰረት ተግባራዊ አድርጋችሁ እንድትሞሉ ፡፡
  17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 36 20 63 65 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  18. ማሳሳቢያ መስሪያ ቤቱ ከጠቅላላ ድምር ዋጋ 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡       

የጃዊ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here