የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቻግኒ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ (ስቴሽነሪ) እቃዎች፣ ሎት2. ቋሚ አላቂ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት3. የጽዳት እቃዎችን፣ ሎት4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት5. የህንጻ መሳሪያ እቃዎች፣ ሎት6. የመብራት እቃዎች፣ ሎት7. የስፖርት እቃዎች እና አልባሳቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00 (አንድ መቶ አምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ከቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ በመግዛት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት የጽህፈት መሳሪያ (ስቴሽነሪ) እቃዎች 60,000.00 (ስልሳ ሽህ ብር ብቻ)፤ ሎት2. ቋሚ አላቂ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች 37,670.00 (ሰላሳ ሰባት ሽህ ስድስት መቶ ሰባ ብር)፣ ሎት 3. የጽዳት እቃዎችን 35,255.00(ሰላሳ አምስት ሽህ ሁለት መቶ አምሳ አምስት ብር)፣ ሎት4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 21,200.00 (ሃያ አንድ ሽህ ሁለት መቶ ብር ብቻ)፣ ሎት5. የህንጻ መሳሪያ እቃዎች 13,700.00 (አስራ ሶስት ሽህ ሰባት መቶ ብር ብቻ)፣ ሎት6. የመብራት እቃወች 10,000.00 (አስር ሽህ ብር)፣ ሎት7. የስፖርት እቃዎች እና አልባሳቶች 12,100.00 (አስራ ሁለት ሽህ አንድ መቶ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ /መሂ-1/ ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊውን ተለይቶ ውል ከተያዘ በኃላ በራሱ ወጭ እስከ ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፤ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ፋይናንስ ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ ጨረታው ከወጣበት በ21 ኛው ቀን ከጠወቱ 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ አድርጎ መመለስ አለበት፡፡
- የአብክመ ግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 በተጨማሪ የተሻሻሉ እና የተጨመሩ መመሪያዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ ፡፡
- ተጫራቶች ለግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት በተሞላው ጥቅል ድምር ዋጋ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 225 17 21/058 225 16 31 በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡
የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

